Directorate of Driver and Vehicle Qualification
- Home
- የእኛ አገልግሎቶች
- Directorate of Driver and Vehicle Qualification
የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎቶች
የቴክኒክ ብቃት ያረጋገጡ ተሸከርካሪዎች ቦሎ ለመውሰድና ለጠፋባቸው ምትክ ለመውሰድ የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የተሽከርካሪ ምርመራ ውጤት ሰርተፍኬት አያይዞ ማቅረብ
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ (ኮድ 1 እና ኮድ 3)ሲሆን አያይዞ ማቅረብ
- ከፋይናንስ ክሪላንስ (ኮድ 1 እና ኮድ 3)ሲሆን አያይዞ ማቅረብ
- 3ኛ ወገን /ኢንሹራንስ/ የታደሰ አያይዞ ማቅረብ
- የመንገድ ፈንድ ከፖሰታ ቤት የታደሰ አያይዞ ማቅረብ
ቦሎ ለጠፋባቸው ምትክ ለመውሰድ የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- ቦሎ እንደጠፋበትና ምትክ መጠየቂያ ማመልከቻ ማቅረብ አያይዞ ማቅረብ
- ሊብሬ አያይዞ ማቅረብ
- 300 ብር ክፍያ መፈጸም
የተሸከርካሪ ፋይልን ወደ ሌላ ክልል የማዛወር አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ አመልካቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- ሁለት ጉርድ ፎቶ
- የተሸከርካሪው ባለቤት መታወቂያ ኮፒ እና ሊብሪ አያይዞ ማቅረብ
- በተወካይ ከሆነ ሁለት ቴንብር
- የተወካይ መታወቂያ ኮፒ እና የውክልና ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
- ከፋይናንስ ክሪላንስ(ኮድ1 ፣ ኮድ 3 እና ለኢት ኮድ 3)ሲሆን አያይዞ ማቅረብ
- የዘመኑን አመታዊ ምርመራ ቦሎ ማድረግ
የሰሌዳ ለውጥ ማድረግ ለሚያደርግና ብቃት ማረጋገጫ ለመውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የተሽከርካሪ ባለቤት መታወቂያ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- በተወካይ ከሆነ መታወቂያ ኮፒ እና የውክልና ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
- ከፖሊስ መረጃ ከወንጀል ነፃ ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
- ከፋይናንስ ክሪላንስ አያይዞ ማቅረብ
- ተሽከርካሪውን ይዘው መቅረብ
የጋራዥ አገልግሎት ለመስጠት ለሚፈልጉ ደንበኞች አዲስ ፍቃድ ለመውሰድና የማደስ አገልግሎት ለማግኘት አመልካቾች የሚከተሉትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- አመልካቹ በ6 ወር ጊዜ ውሰጥ የተነሳው 2 ጉርድ ፓሰፖርት መጠን ባለቀለም ፎቶግራፍ ማቅረብ
- የአመልካቹን ማንነት የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፀና የፓስፖርት ኮፒ ማቅረብ ወይም የአሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ያቀርባል አያይዞ ማቅረብ
- የንግድ ድርጅቱ ሙሉ አድራሻ ክልል፣ ዞን፡ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ ቀበሌ የስልክ ቁጥር፣ፖስታ ሳጥን ቁጥር፣ፋክስና ኢሜል ካለ
- የድርጅቱ ባለቤት ወይም ስራ አስኪያጅ ስም እስከ አያት እና አድራሻ
- የባለቤትነት ወይም ስራ አስኪያጅ ስም እስከ አያት እና አድራሻ
- እድሜ 18 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ
- አስፈላጊውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም
- ህጋዊ የመሬት የዞታ ማረጋገጫ ካርታና ኢንቨስትመንት ፈቀድ ወይም የመጋዘንና የመስሪያ ቦታ ካርታና ተሻሽሎ የቀረበው የተሽከርካሪ ጥገናና አካል ለውጥ ጋራዥ አገልግሎት መስጫ መስፈርት (STANDARD) ቁጥር---/2011 ዓ.ም መሠረት የባሌቤትነት ማረጋገጫ/በኪራ ከሆነ ህጋዊ የክራይ ውል ማስረጃ/ የሃይማኖት ተቋማት ከሆነ በመሀተም የተረጋገጠ/ሰነድ አልባ ሆኖ የሚመለከተው አካል የካርታ ሂደት ላይ መሆኑን የተገለፀበትን አያይዞ ማቅረብ
- ተሻሽሎ በቀረበውየተሽከርካሪ ጥገናና የአካል ለውጥ ገራዥ አገልግሎት መስጫ መስፈርት(STANDARD) ቀጥር---/2011 ዓ.ም መሰረት ለደረጃው የተሟላ የሰው ሀይልና የትምህርት ማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ በድርጅቱ ማህተም በማረጋጋጥ ከማመልከቻ ጋር አያይዞ ማቅረብ
- የክፍያ መጠን
- ብቃት ማረጋገጫ ሲወስድ 1000ብር
- ብቃት ማረጋገጫ ለማደስ 500 ብር
- ለጠፋ ወይም ለተበላሸ 200 ብር
የተሸከርካሪ ምርመራ ተቋም ውክልና ለመውሰድ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የሥራ አስኪያጁ/ባለቤት/ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- የተቋም የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- የባለ ይዞታ ካርታ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ዘንድ የፀደቀ የቤት ክራይ ውል ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- በተቋሙ/ባለቤቱ/ ስም የተመዘገበ ዘመናዊ የምርመራ መሳሪያ ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- የሙያ ብቃት ሰርተፍኬት ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- የክፍያ መጠን
- ለመጀመሪያ ጊዜ ሲወስድ 5000 ብር
- በየአመቱ እድሳት ሲያደርግ
- ደረጃ 1 2000 ብር
- ደረጃ 2 3000 ብር
- ደረጃ 3 4000 ብር
- ደረጃ 4 5000 ብር
የተሽከርካሪ አስመጪ ድርጅት/ግለሰቦች ፍቃድ ለመውሰድና ለማደስ ማሟላት ያለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- Agent from the manufacturer company only for importers importing new vehicles
- Attach Letter of Authorization
- Only for importers importing a new vehicle from the manufacturing company
- Attaching a Chamberized certificate
- If the information obtained in turn 1 and 2 is outside of Ethiopia, the Ministry of Foreign Affairs of the Government of Ethiopia
- Attaching the document of authentication
- Only for importers importing a new vehicle, the vehicle must be no more than 2 years old
- The vehicle that the importer claims to provide must be free from the country’s climate and topography as well as environmental pollution free.
- Obligation to provide sufficient and reliable spare parts for the vehicle
- According to the requirements set by the authority, the workshop facility and human resources should be in sufficient condition.
- Providing proof of the availability of sufficient vehicle parking and work space according to the requirements issued by the authority
- Original brochures and technical specification written in English
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎቶች
ነባር/የቀድሞ/ መንጃ ፈቃድ ለማደስ የሚጠይቁ ባለጉዳዩች የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
- የደም አይነት አያይዞ ማቅረብ
- 3 x 4 ፎቶ አያይዞ ማቅረብ
- ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር
አዲሱን መንጃ ፈቃድ ለማሰደስ መሟላት ያለበት መረጃ
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
- የደም አይነት አያይዞ ማቅረብ
- ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680
የእድሳት ጊዜው ያላፈበት መንጃ ፈቃድ ለማደስ መሟላት ያለበት መረጃ
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
- ከደም አይነት አያይዞ ማቅረብ
- አንድ ጉርድ ፎቶ አያይዞ ማቅረብ
- የፈተና ክፍያ 200 ብር
- የእድሳት ውዝፍ ክፍያ ________
- የተግባር ፈተና በአካል ቀርቦ መፈተን አለበት
ለመንጃ ፍቃድ ኢንተርናሽናል ደብዳቤ ለማፃፍ ማሟላት ያለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- ሁለት ጉርድ ፎቶ
- ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 620
የመንጃ ፍቃድ ወደ ሌላ ክልል ዝውውር ለመጠየቅ ማሟላት ያለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- ከሚኖርበት አካባቢ የነዋሪነት ማስረጃ ማቅረብ(መታወቂያና ደብዳቤ)
- ሁለት ጉርድ ፎቶ
- የአገልግሎት ክፍያ
- ፋይሉን ሙሉ ኮፒ ማድረግ
አዲስ መንጃ ፈቃድ የሚወስዱ አሽከርካሪዎች ማሟላት ያለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የማሰልጠኛ ሰርተፍኬት ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- ለማሰልጠኛ የአገልግሎት ክፍያ የተከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
- ለፈተና የአገልግሎት የከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
- ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር
ልዩ ስልጠና (ማሻሻያ) ለሚወስዱ አሽከርካሪዎች ማሟላት ያለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
- የማሰልጠኛ ሰርተፍኬት ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- የትምህርት ማስረጃ ኡርጅናልና ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
- መንጃ ፈቃድ አያይዞ ማቅረብ
- ለማሰልጠኛ አገልግሎት ለማግኘት የከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
- ለፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
- ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር
የውጪ አገር መንጃ ፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ አቻ ለመቀየር ማሟላት ያለባቸው
- የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
- ከውጪ ጉዳይ ስለትክክለኛነቱ የተረጋገጠበትን ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
- ሰነዶች ማረጋገጫ ማረጋገጥ አያይዞ ማቅረብ
- ከእንግሊዝኛ ውጪ ከሆነ ማስተርጎም
- መንጃ ፈቃዱን ይዞ በአካል መቅረብ
- ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር