Directorate of Driver and Vehicle Qualification admin ሰኔ 7, 2024

የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎቶች

የቴክኒክ ብቃት ያረጋገጡ ተሸከርካሪዎች ቦሎ ለመውሰድና ለጠፋባቸው ምትክ ለመውሰድ የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፡፡

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. የተሽከርካሪ ምርመራ ውጤት ሰርተፍኬት አያይዞ ማቅረብ
  3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ (ኮድ 1 እና ኮድ 3)ሲሆን አያይዞ ማቅረብ
  4. ከፋይናንስ ክሪላንስ (ኮድ 1 እና ኮድ 3)ሲሆን አያይዞ ማቅረብ
  5. 3ኛ ወገን /ኢንሹራንስ/ የታደሰ አያይዞ ማቅረብ
  6. የመንገድ ፈንድ ከፖሰታ ቤት የታደሰ አያይዞ ማቅረብ

ቦሎ ለጠፋባቸው ምትክ ለመውሰድ የሚከተሉትን ማቅረብ አለባቸው፡፡

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. ቦሎ እንደጠፋበትና ምትክ መጠየቂያ ማመልከቻ ማቅረብ አያይዞ ማቅረብ
  3. ሊብሬ አያይዞ ማቅረብ
  4.  300 ብር ክፍያ መፈጸም

የተሸከርካሪ ፋይልን ወደ ሌላ ክልል የማዛወር አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ አመልካቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. ሁለት ጉርድ ፎቶ
  3. የተሸከርካሪው ባለቤት መታወቂያ ኮፒ እና ሊብሪ አያይዞ ማቅረብ
  4. በተወካይ ከሆነ ሁለት ቴንብር
  5. የተወካይ መታወቂያ ኮፒ እና የውክልና ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
  6. ከፋይናንስ ክሪላንስ(ኮድ1 ፣ ኮድ 3 እና ለኢት ኮድ 3)ሲሆን አያይዞ ማቅረብ
  7. የዘመኑን አመታዊ ምርመራ ቦሎ ማድረግ

የሰሌዳ ለውጥ ማድረግ ለሚያደርግና ብቃት ማረጋገጫ ለመውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. የተሽከርካሪ ባለቤት መታወቂያ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  3. በተወካይ ከሆነ መታወቂያ ኮፒ እና የውክልና ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
  4. ከፖሊስ መረጃ ከወንጀል ነፃ ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
  5. ከፋይናንስ ክሪላንስ አያይዞ ማቅረብ
  6. ተሽከርካሪውን ይዘው መቅረብ

የጋራዥ አገልግሎት ለመስጠት ለሚፈልጉ ደንበኞች አዲስ ፍቃድ ለመውሰድና የማደስ አገልግሎት ለማግኘት አመልካቾች የሚከተሉትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. አመልካቹ በ6 ወር ጊዜ ውሰጥ የተነሳው 2 ጉርድ ፓሰፖርት መጠን ባለቀለም ፎቶግራፍ ማቅረብ
  3. የአመልካቹን ማንነት የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፀና የፓስፖርት ኮፒ ማቅረብ ወይም የአሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ያቀርባል አያይዞ ማቅረብ
  4. የንግድ ድርጅቱ ሙሉ አድራሻ ክልል፣ ዞን፡ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ ቀበሌ የስልክ ቁጥር፣ፖስታ ሳጥን ቁጥር፣ፋክስና ኢሜል ካለ
  5. የድርጅቱ ባለቤት ወይም ስራ አስኪያጅ ስም እስከ አያት እና አድራሻ
  6. የባለቤትነት ወይም ስራ አስኪያጅ ስም እስከ አያት እና አድራሻ
  7. እድሜ 18 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ
  8. አስፈላጊውን የአገልግሎት ክፍያ መፈፀም
  9. ህጋዊ የመሬት የዞታ ማረጋገጫ ካርታና ኢንቨስትመንት ፈቀድ ወይም የመጋዘንና የመስሪያ ቦታ ካርታና ተሻሽሎ የቀረበው የተሽከርካሪ ጥገናና አካል ለውጥ ጋራዥ አገልግሎት መስጫ መስፈርት (STANDARD) ቁጥር---/2011 ዓ.ም መሠረት የባሌቤትነት ማረጋገጫ/በኪራ ከሆነ ህጋዊ የክራይ ውል ማስረጃ/ የሃይማኖት ተቋማት ከሆነ በመሀተም የተረጋገጠ/ሰነድ አልባ ሆኖ የሚመለከተው አካል የካርታ ሂደት ላይ መሆኑን የተገለፀበትን አያይዞ ማቅረብ
  10. ተሻሽሎ በቀረበውየተሽከርካሪ ጥገናና የአካል ለውጥ ገራዥ አገልግሎት መስጫ መስፈርት(STANDARD) ቀጥር---/2011 ዓ.ም መሰረት ለደረጃው የተሟላ የሰው ሀይልና የትምህርት ማስረጃቸውን ፎቶ ኮፒ በድርጅቱ ማህተም በማረጋጋጥ ከማመልከቻ ጋር አያይዞ ማቅረብ
  11. የክፍያ መጠን
    1. ብቃት ማረጋገጫ ሲወስድ 1000ብር
    2. ብቃት ማረጋገጫ ለማደስ 500 ብር
    3. ለጠፋ ወይም ለተበላሸ 200 ብር

የተሸከርካሪ ምርመራ ተቋም ውክልና ለመውሰድ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. የሥራ አስኪያጁ/ባለቤት/ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  3. የተቋም የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  4. የባለ ይዞታ ካርታ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ዘንድ የፀደቀ የቤት ክራይ ውል ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  5. በተቋሙ/ባለቤቱ/ ስም የተመዘገበ ዘመናዊ የምርመራ መሳሪያ ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  6. የሙያ ብቃት ሰርተፍኬት ዋናውን እና 1 ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  7. የክፍያ መጠን
    1. ለመጀመሪያ ጊዜ ሲወስድ 5000 ብር
    2. በየአመቱ እድሳት ሲያደርግ
      1. ደረጃ 1 2000 ብር
      2. ደረጃ 2 3000 ብር
      3. ደረጃ 3 4000 ብር
      4. ደረጃ 4 5000 ብር

የተሽከርካሪ አስመጪ ድርጅት/ግለሰቦች ፍቃድ ለመውሰድና ለማደስ ማሟላት ያለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. Agent from the manufacturer company only for importers importing new vehicles 
  3. Attach Letter of Authorization
  4. Only for importers importing a new vehicle from the manufacturing company  
  5. Attaching a Chamberized certificate
  6. If the information obtained in turn 1 and 2 is outside of Ethiopia, the Ministry of Foreign Affairs of the Government of Ethiopia 
  7. Attaching the document of authentication
  8. Only for importers importing a new vehicle, the vehicle must be no more than 2 years old 
  9. The vehicle that the importer claims to provide must be free from the country’s climate and topography as well as environmental pollution free.
  10. Obligation to provide sufficient and reliable spare parts for the vehicle
  11. According to the requirements set by the authority, the workshop facility and human resources should be in sufficient condition.
  12. Providing proof of the availability of sufficient vehicle parking and work space according to the requirements issued by the authority
  13. Original brochures and technical specification written in English

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አገልግሎቶች

ነባር/የቀድሞ/ መንጃ ፈቃድ ለማደስ የሚጠይቁ ባለጉዳዩች የሚከተሉትን ማሟላት አለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
  3. የደም አይነት አያይዞ ማቅረብ
  4. 3 x 4 ፎቶ አያይዞ ማቅረብ
  5. ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር

አዲሱን መንጃ ፈቃድ ለማሰደስ መሟላት ያለበት መረጃ

  • የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  • የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
  • የደም አይነት አያይዞ ማቅረብ
  • ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680

የእድሳት ጊዜው ያላፈበት መንጃ ፈቃድ ለማደስ መሟላት ያለበት መረጃ

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
  3. ከደም አይነት አያይዞ ማቅረብ
  4. አንድ ጉርድ ፎቶ አያይዞ ማቅረብ
  5. የፈተና ክፍያ 200 ብር
  6. የእድሳት ውዝፍ ክፍያ ________
  7. የተግባር ፈተና በአካል ቀርቦ መፈተን አለበት

ለመንጃ ፍቃድ ኢንተርናሽናል ደብዳቤ ለማፃፍ ማሟላት ያለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. ሁለት ጉርድ ፎቶ
  3. ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 620

የመንጃ ፍቃድ ወደ ሌላ ክልል ዝውውር ለመጠየቅ ማሟላት ያለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. ከሚኖርበት አካባቢ የነዋሪነት ማስረጃ ማቅረብ(መታወቂያና ደብዳቤ)
  3. ሁለት ጉርድ ፎቶ
  4. የአገልግሎት ክፍያ
  5. ፋይሉን ሙሉ ኮፒ ማድረግ

አዲስ መንጃ ፈቃድ የሚወስዱ አሽከርካሪዎች ማሟላት ያለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. የማሰልጠኛ ሰርተፍኬት ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  3. ለማሰልጠኛ የአገልግሎት ክፍያ የተከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
  4. ለፈተና የአገልግሎት የከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
  5. ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር

ልዩ ስልጠና (ማሻሻያ) ለሚወስዱ አሽከርካሪዎች ማሟላት ያለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. የአይን ህክምና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ
  3. የማሰልጠኛ ሰርተፍኬት ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  4. የትምህርት ማስረጃ ኡርጅናልና ኮፒ አያይዞ ማቅረብ
  5. መንጃ ፈቃድ አያይዞ ማቅረብ
  6. ለማሰልጠኛ አገልግሎት ለማግኘት የከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
  7. ለፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈለበት ደረሰኝ አያይዞ ማቅረብ
  8. ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር

የውጪ አገር መንጃ ፈቃድ ወደ ሀገር ውስጥ አቻ ለመቀየር ማሟላት ያለባቸው

  1. የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ መሙላት
  2. ከውጪ ጉዳይ ስለትክክለኛነቱ የተረጋገጠበትን ደብዳቤ አያይዞ ማቅረብ
  3. ሰነዶች ማረጋገጫ ማረጋገጥ አያይዞ ማቅረብ
  4. ከእንግሊዝኛ ውጪ ከሆነ ማስተርጎም 
  5. መንጃ ፈቃዱን ይዞ በአካል መቅረብ 
  6. ለአገልግሎቱ የተመደበ የክፍያ መጠን 680 ብር